የእንስሳት እርባታ፡- በእንስሳት እርባታ ልምድ ያካበቱ ቤተሰቦች ከብት በማግኘት ዘላቂ የገቢ ምንጭ እና የምግብ ዋስትናን እንዲያገኙ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
መሳሪያዎች እና ስልጠናዎች፡- በሜካኒክስ፣ አናጢዎች፣ ልብስ ስፌት እና ሌሎችም በመሳሰሉት ሙያዎች የተካኑ ተፈናቃዮች ኑሯቸውን መልሰው እንዲገነቡ፣ ራሳቸውን እንዲችሉ እና ለአካባቢያቸው የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ አስፈላጊ መሳሪያዎችና ግብአቶች ይሟላላቸዋል።